LYRIC

ስሜስ የማነው
ልቤ አብሮኝ ከሌለ
አንቺን ሲጠሩሽ
አፌ አቤት እያለ
እኔ እንደዚህ እስኪነሳኝ ሀገር
ሰው ወድጄ አላውቅም
2x
ከአንዴም ሁለቴ ልቤ ዳግም ወዶ
መቼ አፈቀረ ይህን ያህል ሄዶ
እንዴት አድርጌ ብወድሽ
እኔ አቤት ልበል በስምሽ
ከፍቅር ባሀር ብጠልቅም
እንዲ ሰምቼስ አላውቅም
ከአንዴም ሁለቴ ልቤ ዳግም ወዶ
መቼ አፈቀረ ይህን ያህል ሄዶ
እንዴት አድርጌ ብወድሽ
እኔ አቤት ልበል በስምሽ
ስምሽ ሲጠራ ወይ ካልኩኝ
በሌለሽበት ነበርኩኝ
ስሜስ የማነው
ልቤ አብሮኝ ከሌለ
አንቺን ሲጠሩሽ
አፌ አቤት እያለ
እኔ እንደዚህ እስኪነሳኝ ሀገር
ሰው ወድጄ አላውቅም
2x
በመልክሽ ጸሀይ ሲነጋ ለሊቴ
ድምጽሽ አነቃኝ ከብቸኝነቴ
ሆነሽ የፍቅር ዘማሪ
አቤት እንደ ወፍ ስታምሪ
አይኔ ሲከተል ክንፍሽን
ተገልጦ አየሁት ልብሽን
2x
የመልክሽ ጀንበር ጨለማውን ጥሶ
ድምጽሽ አነቃኝ ማለዳ ቀስቅሶ
ሆነሽ የፍቅር ዘማሪ
አቤት እንደ ወፍ ስታምሪ
አይኔ ሲከተል ክንፍሽን
ተገልጦ አየሁት ልብሽን
በሃሳብ አብሬሽ በራለው
ዞረኔ ሲሉሽ ዞራለው
2x

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO