LYRIC

ካላየሁሽ ይጨንቀኛል ይከፋኛል
እንዲያው ዝም ብሎ ሆድ ይብሰኛል
ካልቻልሽ አንቺ እኔው ልምጣ ልምጣ ልይሽ
ከሚያስጨንቀኝ ብሶ ናፍቆትሽ
ሳላይሽ አልውልም
አይሆንም አልቀርም
ካለሽበት እመጣለሁ
ናፍቀሺኛል አይሻለሁ
ካላየሁሽ ይጨንቀኛል ይከፋኛል
እንዲያው ዝም ብሎ ሆድ ይብሰኛል
ካልቻልሽ አንቺ እኔው ልምጣ ልምጣ ልይሽ
ሐሳብ ጨረሰኝ ብሶ ናፍቆትሽ
ሳላይሽ አልውልም
አይሆንም አልቀርም
ካለሽበት እመጣለሁ ናፍቀሺኛል አይሻለሁ
አዲስ አመል ያነጫንጨኛል
ካላየሁሽ ደርሶ ይከፋኛል
ህመሜን ማን አውቆት የኔን ጭንቀት
ነገር ላይጥመኝ አንቺ የሌለሽበት
ሳቅ ጨዋታሽን ለምጄው ይናፍቀኛል
ያንቺን ባላውቅም ለኔስ አንቺን ያሰኘኛል
ሰው ናፍቄ ችዬ እንዴት ዝም እላለሁ
ሰበብ ፈጥሬ በምክንያት አይሻለሁ
ሳላይሽ አልውልም
አይሆንም አልቀርም
ካለሽበት እመጣለሁ
ናፍቀሺኛል አይሻለሁ
ለብቻው ነው የኔስ ጉዳይ አንቺን ሳጣ
ከሰው አልገጥም ቃል ካፌም አይወጣ
ይባስ ብሎ ደርሶ ይከፋኛል
ፍቅርሽ አይሎ አመሌ ሸሽቶኛል
ሳቅ ጨዋታሽን ለምጄው ይናፍቀኛል
ያንቺን ባላውቅም ለኔስ አንቺን ያሰኘኛል
ሰው ናፍቄ ችዬ እንዴት ዝም እላለሁ
ሰበብ ፈጥሬ በምክንያት አይሻለሁ
ሳላይሽ አልውልም
አይሆንም አልቀርም
ካለሽበት እመጣለሁ
ናፍቀሺኛል አይሻለሁ
ኦ ኦ ኦ……….. ኦ ኦ ኦ ኦ
ኦ ኦ ኦ………..ኦ ኦ ኦ ኦ ኦ
ሳላይሽ አልውልም
አይሆንም አልቀርም
ካለሽበት እመጣለሁ
ናፍቀሺኛል አይሻለሁ
ሳላይሽ አልውልም
አይሆንም አረ አይሆንም
ካለሽበት እመጣለሁ
ናፍቀሺኛል አይሻለሁ

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO