LYRIC

በአይኖቹ ቋንቋ በስስት እያባበለ
ቀርቦ ሲጠራኝ ደጋግሞ ፍቅር እያለ
ባየሁ በሰማሁት ሆነ እንደፈራሁት
እጅ አልሰጥም ብዬ ቀረሁ ተጃጅዬ
ሲችል ሲያቀብጠኝ 2×
እጅ አሰጠኝ
ሲችል ሲያሰንፈኝ 2×
አሸነፈኝ
እያማረኝ ስከተል እምቢ ብልም ጾም ለማደር
ስንት አልምዶኝ እንደዋዛ
በየት በኩል አደብ ልግዛ
ፍቅር ሰቶ ሰው ማገዙን
ያውቅበታ አያያዙን
ቢያስፈራኝም አኳሀኑ አቃተኝ ግን መጨከኑ
ሲችል ሲያቀብጠኝ 2×
እጅ አሰጠኝ
ሲችል ሲያሰንፈኝ 2×
አሸነፈኝ

ሽቅርቅሯ ጎበዜ የኔ ጎበዜ
የፍቅር ወርቅ ነሽ አባዜ
ስሜቴ ረዘምዘም ያለች ቆንጆ ወዛሟ
ለፍቅሯ ታ ታጋሿ የፍቅር ለዛሟ
ነው ከማተቧ የፍቅር ቀለሟ
አልጠላም ካንቺ ጋር መጓዜ መጓዜ
በአይኖቹ ቋንቋ በስስት እያባበለ
ቀርቦ ሲጠራኝ ደጋግሞ ፍቅር እያለ
ባየሁ በሰማሁት ሆነ እንደፈራሁት
እጅ አልሰጥም ብዬ ቀረሁ ተጃጅዬ
ሲችል ሲያቀብጠኝ 2×
እጅ አሰጠኝ
ሲችል ሲያሰንፈኝ 2×
አሸነፈኝ
ሳይታሰብ ልቤ በሩ እየገባኝ መደፈሩ
አለሁ ብሎ እንዳይርቀኝ ነው መውደዴ ያስጨነቀኝ
ፈቅዶ ልቡን ከታደልኩት ያርገው ብቻ እንዳሰብኩት
ህይወት ጣፍጦኝ ለመኖሬ ደስተኛ ነኝ በማፍቀሬ
ሲችል ሲያቀብጠኝ 2×
እጅ አሰጠኝ
ሲችል ሲያሰንፈኝ 2×
አሸነፈኝ

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO