LYRIC

ሲዋደዱ ለካ ደሞ ሲፋቀሩ
አመት ያህላል ወይ ለካ ሲቃጠሩ
2X
እንኳን የወደዱት የለመዱት ሲቀር
ደጅ ደጅ የሚያሳይ ማን አለ እንደ ፍቅር
ቀን መሽቶ እስኪነጋ አመት የሚመስለኝ
ናፍቆትሽ ነው እንጂ ነፍስ የነሳኝ
ጠጋ ብለሽኝ አይኔ ስር
ይነግርሻል አይኔ በፍቅር
እንኳን መጣሽልኝ የኔ ውድ
ከምንወደው ቦታ እንሂድ
የማጣሽ ቢመስለኝ ቆሜያለው ማልጄ
ከቀጠሮ መቅደም ላንቺ ስል ለምጄ
አገር ደጁን ሳይከፍት ሳንቀናው መንቀኑ
ይጠብቅሽ እንጂ አስቀኑ ቀኑ
በላዬ ላይ መቶ ዙሪያዬን ሳማትር
ማለዳ እንደቆምኩኝ ደረሰብኝ ቀትር
ምን ነካው ይለኛል ሀሳብ የሌለበት
ባንቺ ተለክፌ ጠፍቶኝ የቆምኩበት
እንኳን መጣሽልኝ የኔ ውድ
ከምንወደው ቦታ እንሂድ
ጠጋ ብለሽኝ አይኔ ስር
ይነግርሻል አይኔ በፍቅር
እንኳን የወደዱት የለመዱት ሲቀር
ደጅ ደጅ የሚያሳይ ማን አለ እንደ ፍቅር
ቀን መሽቶ እስኪነጋ አመት የሚመስለኝ
ናፍቆትሽ ነው እንጂ ነፍስ የነሳኝ
ጠጋ ብለሽኝ አይኔ ስር
ይነግርሻል አይኔ በፍቅር
እንኳን መጣሽልኝ የኔ ውድ
ከምንወደው ቦታ እንሂድ
የማፍቀሬን ጥግ አሳየሽኝና
አቅሜን አወኩት ዛሬ አጣሁሽና
እየተዋደዱ ዘወትር መቃጠል
መቼም አያክልም ተፋቅሮ እንደመኖር
በላዬ ላይ ነግቶ ዙሪያዬን ሳማትር
ማለዳ እንደቆምኩኝ ደረሰብኝ ቀትር
ምን ነካው ይለኛል ሀሳብ የሌለበት
ባንቺ ተለክፌ ጠፍቶኝ የቆምኩበት
እንኳን መጣሽልኝ የኔ ውድ
ከምንወደው ቦታ እንሂድ
ጠጋ ብለሽኝ አይኔ ስር
ይነግርሻል አይኔ በፍቅር
3X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO