LYRIC

ወደ ሀገሬ መልሰኝ
አንተ ሰማይ (3x)
ከምወደው አይን ለአይን
እንድተያይ (3x)
የሰው ሀገር ኑሮ ምቾቱ እኔ አልደላኝ
በልቼ አልተጠጋኝ ጠጥቼ አላረካኝ
አንተ ሰማይ (3x)
ልቤን አደከመው ትዝታ ናፍቆቴ
በተለይ በተለይ ያ መምህሩ አባቴ
አንተ ሰማይ (2x)
በስልክ አይዞህ ብለው ምንም አላረካኝ
እባክህ አንተ ሰማይ ቤታችን አስገባኝ
አንተ ሰማይ (2x)
የህይወቴን ምሳሌ በማንም ባይተካም
ከአጠገቡ ልሁን በደብዳቤ አይበቃም
አንተ ሰማይ (6x)
ከጎኑ መሆን እፈልጋለሁ
እጆቹን ይዤ አይኑን እያየሁ
የእኔ ልጅ ሲለኝ አቤት አባቴ
ፈገግ ሲልልኝ ታየኝ ኩራቴ
ይሄ ነው ደስታ ይሄ ነው አለም
ከቤት ርቆ እርካታ የለም
አንተ ሰማይ (12x)
ወደ ሀገሬ መልሰኝ
አንተ ሰማይ (3x)
ከምወደው አይን ለአይን
እንድተያይ (3x)
የሰው ሀገር ኑሮ ምቾቱ እኔ አልደላኝ
በልቼ አልተጠጋኝ ጠጥቼ አላረካኝ
አንተ ሰማይ (3x)
ሳይሰስት የሰጠኝ ጊዜውን ህይወቱን
እስኪ ልድረስለት ልዳብሰው ሽበቱን
አንተ ሰማይ (2x)
እሱ እየደከመ እኔን አርጎኛል ሰው
እስቲ ልድረስለት ተራዬን ልካሰው
አንተ ሰማይ (2x)
እንደ ሻማ ቀልጦ ብርሀን የሰራብኝ
ከአጠገብህ ልሁን ዉለታዉ አለብኝ
አንተ ሰማይ (6x)
ከጎኑ መሆን እፈልጋለሁ
እጆቹን ይዤ አይኑን እያየሁ
የእኔ ልጅ ሲለኝ አቤት አባቴ
ፈገግ ሲልልኝ ታየኝ ኩራቴ
ይሄ ነው ደስታ ይሄ ነው አለም
ከቤት ርቆ እርካታ የለም
አንተ ሰማይ (12x)

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO