LYRIC

ምን አለ አንቺ ልጅ ምን አለ 2X
ሁኔታውን አይተሸ እንደሚወድሽ አውቀሽ
ሁሉንም ገምተሽ ብትወጅው ምንአለ
2X
ጥሩ ነው በፍቅር ጥሩ መሆን ጥሩ ነው
እኔ ባንቺ በያዘኝ ግፍ ነው
ያስተዛዝበናል ጥሩ ነው
ያቀያይመናል
2X
እንቅልፍ በአይኔ ሳይዞር ይነጋል ለሊቱ
ከብቶች ሳይሰማሩ እኔ በጠዋቱ
ቤትሽ እመጣለው ደጃፍ እቆማለው
ላይ ታቹን አያለው
ልጆች አስጠራለው
እንቆራጠጣለው
ልጆቹም ሄደው በዛው ይቀራሉ
አይኖቼ ከመጣው ከሄደው ይንቀዋለላሉ
ጠብቄ ጠብቄሽ ሳጣሽ ግን እሄዳለው
አላስችል ብሎኝ ደግሞ እመለሳለው
ቤትሽን ቤትሽን እምለከታለው
ምን አለ አንቺ ልጅ ምን አለ 2X
ሁኔታውን አይተሸ እንደሚወድሽ አውቀሽ
ሁሉንም ገምተሽ ብትወጅው ምንአለ
2X
ጥሩ ነው በፍቅር ጥሩ መሆን ጥሩ ነው
እኔ ባንቺ በያዘኝ ግፍ ነው
ያስተዛዝበናል ጥሩ ነው
ያቀያይመናል
2X
ደግሞ በማግስቱ ተስፋ አደርጋለው
ካንቺ ጋር ልጫወት በሀሳብ አልማለው
ደብዳቤ ጽፋለው
ቃላት እመርጣለው
ብዙ እጨነቃለው
ስልክ እደውላለው 2X
ስልኩም የመያዝ ምልክት ያሰማኛል
ደብዳቤ እንዳልጽፍ ቃላቶች ያጥሩኛል
መልሼ መልሼ ደውላለው
አሁንም መልሼ ሞክራለው
ብዬ ብዬ ሳጣሽ በንዴት በግናለው
ምን አለ አንቺ ልጅ ምን አለ 2X
ሁኔታውን አይተሸ እንደሚወድሽ አውቀሽ
ሁሉንም ገምተሽ ብትወጅው ምንአለ
2X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO