LYRIC

ናፈቀኝ ናፈቀኝ ሀገሬ
የትውልድ መንደሬ
ተሰማኝ ተሰማኝ ድምጽሽ
የድሬ አድባር ነሽ
ልሂድ እኔም ወደ ሀረር ከደጎቹ ሀገር
የሀረር የሀረር አባድር ጾምም አያሳድር
አቦ በሉኝ ግቢ በሉኝ 2X
ያሰኘኝ አቦል አቦል እንጂ
ምን ያደርጋል ቶናው ትዝታው
አይጠፋም ከፊቴ የጠጣሁት ቡና
ምን ነበር ምነው በቀረብኝ
ባልቀመስኩ አቦሉን ወግ ልማድ የለኝ
ባልችል አዋዋሉን
ውሰጂኝ ወተራይ ናፈቀኝ ሀገሬ
ያኔ እንደወሰድሽኝ መልሽኝ መንደሬ
ብቅ አለ ከማዶ ተሰማ ጥሩንባ
የጅቡቲ ባቡር መጣ ከእንጆ ገባ
ነጭ ሽርጥ ታጥቆ ጊሬል እንዳሰረ
ቆሞ የሚጠብቀኝ ጊሊሌ ነበረ
የእኔ ወዳጅና የእቃው ተረካቢ
ድሬ ይጠብቁኛል ጅቡ ሳይጮህ ግቢ
ይላሉ ድሬዎች እንግዳ ሲመጣ
አቦ ማሻላ ነው ግቢ ወደ ቤት
ይላሉ ሀረሮች እንግዳ ሲመጣ
አቦሉ ላይ ደረሽ ግቢ ወደቤት ሀ
ማሻላህ ነው የሀገሬ ሰው
ሩሩህ ነው ለወደደው
ረሀ ነው ምድረ አፈሩ
የሚያላምድ ሀረር ፍቅሩ
ሰላም ሁኑ ባጋደሮ
ማሻላ ናት ድሬደዋ
ህዝቧም እኮ ውሎ አዳሩ
ማሻላ ነው አዋዋሉ
አቦ ሰላም ይመቻቹ
ሀረር ላይ ነን አይክፋቹ
ሀቅም አለው የሀገሬ ሰው
ግልጽ እኮ ነው ለተመቸው
ጭንቅም አያውቅ ለተመቸው
አብሮ በልቶ ነው ያደገው
አቦ በሉኝ ግቢ በሉኝ 2X
ያሰኘኝ አቦል አቦል እንጂ
ምን ያደርጋል ቶናው ትዝታው
አይጠፋም ከፊቴ የጠጣሁት ቡና
ምን ነበር ምነው በቀረብኝ
ባልቀመስኩ አቦሉን ወግ ልማድ የለኝ
ባልችል አዋዋሉን
መስከቲ እጣኑን ድሪያ ጎገራው
ላስረክበው ሄጄ ሳይመሽ ደርዘን ተራው
ተጓድም ደርሼ ወደ ቤት ስገባ
ያኔ ማሻላ ነው በሉኝ መረሀባ
ለሩዝ ተራ ታይዋን ለአሸዋ መንደሩ
አይቀርም ቅርብ ነው ጅቡቲ ወደቡ
የመርከብ በረከት የባቡሩ ሲሳይ
ማሻላ ነው አልኩኝ ድሬ ገብቼ ሳይ
በሬዱ ማሻላ ኩሩ በደን ቀሽቲ
ተውበሽ ደምቀሻል አምሮብሻል እስቲ
ቢሻን ቀበላዋ ያለኮረስማ
ጠጣሁኝ በቀለስ ውሀ እንኳን ሲጠማ
ማሻላህ ነው የሀገሬ ሰው
ሩሩህ ነው ለወደደው
ረሀ ነው ምድረ አፈሩ
የሚያላምድ ሀረር ፍቅሩ
ሰላም ሁኑ ባጋደዋ
ማሻላ ናት ድሬደዋ
ህዝቧም እኮ ውሎ አዳሩ
ማሻላ ነው አዋዋሉ
የባቡሩ ውለታሽ
ድሬ ስንቱን አበቀልሽ
ያ መዓዛው ጠረንሽ
የመስከቲው እጣንሽ
የሙሸበቅ የባቅላባው
ድሬ ላይነው መፈጠሪያው 2X
ድሬ ላይ ነው ያው መገኛው

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO