LYRIC

ስለእኔ የሆነውን ይናገር
በዚች ምድር ላይ በህይወት እስካለው
ብደሰት ብራብ ብጠማም
ከዛኛው አለም መች እቀራለው
2X
በድንገት ለምትቀር አለም ምን ያስጨንቃል
ምን ያስጨንቃል
ምን ያስጨንቃል
የዛሬን እንጂ የነገን እስኪ ማን ያውቃል
ማን ያውቃል
ተው ልቤን አታስጨንቀኝ እንዲያው በተስፋ
እንዲያው በተስፋ
በቁሙ ጠዋት ያየሁት ማታ እየጠፋ
ማታ ሲጠፋ
ስንቱ ባጭር ሲቀር እያየው እየተረታ
በተራዬ ለምን ይዋሸኝ የጠራኝ ለታ
ለመንገዴ ስንቅ ሳልሰንቅ ለዛኛው ቤቴ
ተነስ ብባል መች ያስቀረኛል ሀብት ንብረቴ 2X
ስለእኔ የሆነውን ይናገር
በዚች ምድር ላይ በህይወት እስካለው
ብደሰት ብራብ ብጠማም
ከዛኛው አለም መች እቀራለው
2X
የጸና መከራውንም አይቼዋለው
አይቼዋለው
ሁሉንም እኔስ በትግስት አልፌዋለው
አልፌዋለው
ክፉንም ደጉንም ነገር አሳይቶኛል
አሳይቶኛል
እንግዲህ ለቀሪው አለም ምን ያጓጓኛል
ምን ያጓጓኛል
ስንቱ ባጭር ሲቀር እያየው እየተረታ
በተራዬ ለምን ይዋሸኝ የጠራኝ ለታ
ለመንገዴ ስንቅ ሳልሰንቅ ለዛኛው ቤቴ
ተነስ ብባል መች ያስቀረኛል ሀብት ንብረቴ 2X
ምን ቢያምሩ ለብሰው ቢያጌጡ ቢሽቀረቀሩ
ቢሽቀረቀሩ
በተስፋ ቆመናል ከንቱ እዛ ላይቀሩ
እዛ ላይቀሩ
ባዳ ነው እንዳማረ አይኖር ገላም ይከዳል
ገላም ይከዳል
ከአፈሩ አንስቶ ለአፈር ያለማምዳል
ያለማምዳል
ማረፍ ላይቀር በዚች ምድር ላይ ተንኮል ባንሰራ
ተንኮል ባንሰራ
እናይ ነበረ ፍጻሜውን ያምላክን ስራ
የእውነቴን መንገድ ለቅቄ መች እጓዛለው
እኔው ለእኔው የሚበጀኝን እኔ አውቃለው 8X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO