LYRIC

በአፍላው ንፋስ ፍቅሯ
ከፍ ብዬ ስበር
ክንፌን ሰብራው ሄዳ ለመረፍ ስቸገር
እንደኔ ሰው ወዶ ማጣትን ያልቀመሰው ያልቀመሰው
እርሳት ተዋት ይለኛል አይ መሬት ያለ ሰው
(አይ መሬት ያለ ሰው) 6X
ተከተለኝ ብላ በፍቅሯ ነካክታኝ
እንዳልበር እንደላርፍ ሚዛን አሳጥታኝ
(አዬ ሰው መሬት ያለ ሰው) 2X
ክንፉን የተመታው ገና በጅማሬው
ማልዶ አይገሰግስ መች ሊያምር ዝማሬው
(አዬ ሰው መሬት ያለ ሰው)
አዬ ሰው እርሳት አለኝ ጉድ ነው
ስሟን እየጠራው አለው ሲለኝ ሀገሩ
ሆድ ለባሰው ማጭድ ሆነብኝ ነገሩ
(አዬ ሰው መሬት ያለ ሰው)
አዬ ሰው እርሳት አለኝ ጉድ ነው
የዘንድሮ አዋቂ ጨዋ ባደባባይ
ጸሀይ ይሁን ይላል የጨለመበት ሲያይ
(አዬ ሰው መሬት ያለ ሰው)
አዬ ሰው እርሳት አለኝ ጉድ ነው
ደምብሮበት ባይቆም ቸግሮት መዳኛው
ዳር ይዞ ላይረዳው ሲመክረው አፈኛው
አዬ መሬት ያለ ሰው አለ ፈረሰኛው
አይ መሬት ያለ ሰው……..አዬ ሰው
ሞልቶለት የተኛው……..አዬ ሰው
ጎጆ የቀለሰው……..አዬ ሰው
አይ መሬት ያለ ሰው……..አዬ ሰው
ደርሶበት ያላየው……..አዬ ሰው
መፍረድ የቀለለው……..አዬ ሰው
አይ መሬት ያለ ሰው……..አዬ ሰው 3X
አዬ ሰው 3X
በአፍላው ንፋስ ፍቅሯ ከፍ ብዬ ስበር
ክንፌን ሰብራው ሄዳ ለማረፍ ስቸገር
እንደኔ ሰው ወዶ ማጣትን ያልቀመሰው ያልቀመሰው
እርሳት ተዋት ይለኛል አይ መሬት ያለ ሰው
(አይ መሬት ያለ ሰው) 6X
ለፍቅሯ በኖርኩኝ ክዳኝ እንደዘበት
ከደሙ ንጹህ ነኝ ስትል እያመኗት
(አዬ ሰው መሬት ያለ ሰው)
አዬ ሰው እርሳት አለኝ ጉድ ነው
ልይሽ እያረርኩኝ ስትቀልጂ በአይኔ
ይመችሽ ግድ የለም እስኪነጋ ለኔ
(አዬ ሰው መሬት ያለ ሰው)
አዬ ሰው እርሳት አለኝ ጉድ ነው
ቦግ ስል ስትቃጠል እሷን ሳስታውሳት
ስንት ጊዜ ሞትኩት የልቤን ፍም እሳት
(አዬ ሰው መሬት ያለ ሰው)
አዬ ሰው እርሳት አለኝ ጉድ ነው
እዚ እያነደደች እዛ ጋ ማብረዷ
እንዲህ አይደለም ወይ የዚች አለም ፍርዷ
(አዬ ሰው መሬት ያለ ሰው)
አዬ ሰው እርሳት አለኝ ጉድ ነው
ደምብሮበት ባይቆም ቸግሮት መዳኛው
ዳር ይዞ ላይረዳው ሲመክረው አፈኛው
አዬ መሬት ያለ ሰው አለ ፈረሰኛው
ሞልቶለት የተኛው……..አዬ ሰው
ጎጆ የቀለሰው……..አዬ ሰው
አይ መሬት ያለ ሰው……..አዬ ሰው
ደርሶበት ያላየው……..አዬ ሰው
መፍረድ የቀለለው……..አዬ ሰው
አይ መሬት ያለ ሰው……..አዬ ሰው 3X
አዬ ሰው 5X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO