LYRIC

ይከተልሀል ሀሳቤ ትዝታን ሰንቆ 2x
አልጠፋም ፍቅሬ እንዳንተ ከሰፈሬ ርቆ 2x
በማለዳ መገኘት የእዳ ጉዳይ ነው እንጂ
በጠዋት ምን ይሰራል በሀሳብ እኔ ደጅ
ልወጣ ስል ከቤቴ እጠበቀኝ ከበሩ
አልቀነሰም አሁንም ናፍቆቴ ልቤን መስበሩ
ዘመኔን ባንተ ፍቅር ገፍቼው
ቀረው ውሌን አጥቼው
2x
ተው መላ በለኝ 2x
ናፍቆት አንዳንዴ በሀሳብ ገደለኝ
ያንተ ትዝታ ወረተኛው
እያለ ጎኔን አላስተኛው
ፍቅርህ ቀስቅሶ ይረብሸኛል
እንቅልፌን አጣሁ ምን ይሻለኛል
እንዳጠፋኧኝ ምነው ብትረሳኝ
ባለፈው ፍቅር ከምታሳሳኝ
ይከተልሀል ሀሳቤ ትዝታን ሰንቆ 2x
አልጠፋም ፍቅሬ እንዳንተ ከሰፈሬ ርቆ 2x
ያልሆንኩልህ ምን ነበር ተንሰፍስፌልህ ከአንጀቴ
ባዶ አንደበት ቢኖረው በነገረህም አንጀቴ
በቃልቂዳንህ ታስሬ የእውነት ስሰጥህ
አንተ ግን ሚስጥር ይዘህ ትደብቅ ነበር በውስጥህ
እርቀህ ከቀረብኝ ጨዋታ
ምን ያረጋል ትዝታ
2x
ተው መላ በለኝ 3x
ከሀሳብ ገላግለኝ
አታደናግረኝ ግራ አታጋባኝ
ምንድነው በሀሳብ የምታባባኝ
ሆዴን ስትበላ ውለህ አድረሀል
ደግሞ ከእንግዲህ ምን ይቀርሀል
እንዳጠፋኧኝ ምነው ብትረሳኝ
ባለፈው ፍቅር ከምታሳሳኝ
በፍቅር ጊዜ ጥሩ አለም አይተን
የምን ሀሳብ ነው ከርመን ቆይተን

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO