LYRIC

ፍቅር ያለወትሮው ያለቦታው ገብቶ
ያነጫንጨኛል አዬ መላዬ መላው ጠፍቶ
በህግ አምላክ ፍቅር አደብ ግዛ
አሳቤን ቀያይረህ አሀ አታሳጣኝ ለዛ
ቢጠፋኝ ነው መላው
መላው ቢጠፋኝ ነው መላው 2X
ፍቅር አሸነፈን ጀግናው
መላው ቢጠፋኝ ነው አመሌ 3X
ለፍቅር ሰከረ መባሌ
የልቤን ልነግርሽ ደፍሬ
አልቻልኩም ከበደኝ ፍቅርዬ
ፍቅርሽ እንቅልፍ አሳጥቶኛል
መላ በይኝ ፍቅሬ ጨንቆኛል
አሎጣ አለኝ ገብቶ ትዝታ
እያመሰኝ ማታ ማታ
እንደምን ልሁነው ገላዬ
መውደድሽ በረታ በላዬ
በላዬ በላዬ 6X
ፍቅር ያለወትሮው ያለቦታው ገብቶ
ያነጫንጨኛል አዬ መላዬ መላው ጠፍቶ
በህግ አምላክ ፍቅር አደብ ግዛ
አሳቤን ቀያይረህ አሀ አታሳጣኝ ለዛ
ቢጠፋኝ ነው መላው
መላው ቢጠፋኝ ነው መላው 2X
ፍቅር አሸነፈን ጀግናው
መላው ቢጠፋኝ ነው አመሌ 3X
ለፍቅር ሰከረ መባሌ
ገጸበረከቴ ነሽና
ድምቀቴ ኑሮዬ ፋና
ከለገሰኝማ ጌታዬ
በአንቺ ላይ ይጠቅለል ደስታዬ
አይቀርም አንድ ቀን አምናለው
ፍቅርዬ የኔ አደርግሻለው
ሰጥቻለው ለእሱ ህይወቴን
አይነሳኝም መቼም መላዬን
መላዬ መላዬ 2
6X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO