LYRIC

ከመከም ነው ልጁ ጎፈሬ
ያውም ውብ አይናማ ሸበላ ሸበላ
2X
ዛሬም ውደጅው ይለኛል
ነገም ውደጅው ይለኛል
አቤት ቆንጅናው ማማሩ
ተማርኬያለው በፍቅሩ
ሲሄድ ሲመጣ ጠብቄ
አየት አርጌ ሰርቄ
ተረፈኝ በሩቅ መገረም
አቅም አጥቼ ለመቅረብ
ልንገርህ እስኪ ልንገርህ ልንገርህ 4X
ልቤ እስርህ ንፍንፍ
እርብሽብሽ አለብኝ
እንደው ምን ቀን ጥሎት
አይኔ አንተን አየብኝ
ኧረ ተው ኧረ ተው
አንተ አማላይ ኩሩ
ስቀርብህ ቅረበኝ
ከማይህ በሩቁ
ከመከም ነው ልጁ ጎፈሬ
ያውም ውብ አይናማ ሸበላ ሸበላ
2X
እውነት እውነቱን ልንገርህ
የልቤን ፍቅር ላብስርህ
ስንቴ ፈልጌ ተዋለው
አንተ ፊት እፍረት አጣለው
ቀኑስ ይመሻል ይነጋል
ያለሰው መኖር ላይቻል
አይቶ እንዳላየ ብታልፈኝ
ወዶ መቸገር ተረፈኝ
ልንገርህ እስኪ ልንገርህ ልንገርህ 4X
ልቤ እስርህ ንፍንፍ
እርብሽብሽ አለብኝ
እንደው ምን ቀን ጥሎት
አይኔ አንተን አየብኝ
ኧረ ተው ኧረ ተው
አንተ አማላይ ኩሩ
ስቀርብህ ቅረበኝ
ከማይህ በሩቁ

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO