LYRIC

ልኑር……
ካንተ ጋራ ልኑር
ትሁን…..
አለም ሙሉ ትሁን
2X
ላስበበት እንዳትለኝ አሁን
እሺ በለኝ ፍቀድ ያንተ ልሁን
እኔ ታግዬ አንተ አሸነፍከኝ
ጉልበቴ እስኪዝል አብረከረከኝ
ልበ ሙሉ ነህ አድንቄያለው
አብረን እንኑር አፍቅሬሀለው
ከእቅፍህ ከተህ ካላሳረፍከኝ
ከልብህ ጎጆ ካላሳደርከኝ
ማረፊያ ያጣች ወፊቷን ሆኜ
እንዳልቀርብህ የትም ባክኜ
ተማርኬ እጄን ሰጥቼህ
ተጋለጥኩኝ ልቤን አጥቼ
ስከንፍልህ ስበር አፍቅሬህ
አሳርፈኝ ልሁን አብሬህ
ልኑር……
ካንተ ጋራ ልኑር
ትሁን…..
አለም ሙሉ ትሁን
2X
ላስበበት እንዳትለኝ አሁን
እሺ በለኝ ፍቀድ ያንተ ልሁን
ፍቅሬን አምቄ አክርሜዋለው
ዛሬ አልችል ብዬ ተሸንፌያለው
ብዙ ታግሼ አግኝቼአለው
አታስጨንቀኝ ወድጄአለው
ከእቅፍህ ከተህ ካላሳረፍከኝ
ከልብህ ጎጆ ካላሳደርከኝ
ማረፊያ ያጣች ወፊቷን ሆኜ
እንዳልቀርብህ የትም ባክኜ
ቤቴ አስጠላኝ ከበደኝ ደጄ
ግራ ገባኝ አንተን ወድጄ
መጥቻለው ይኧው አፍቅሬህ
ተቀበለኝ ልሁን አብሬህ
ተማርኬ እጄን ሰጥቼህ
ተጋለጥኩኝ ልቤን አጥቼ
ስከንፍልህ ስበር አፍቅሬህ
አሳርፈኝ ልሁን አብሬህ

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO