LYRIC

ዓይኖቼ አያዩ ብርሃን የላቸው
በልጅነቴ ድሮ አጥቼያቸው
ልቤን ተሰማው እንግዳ ነገር
ምርኩዝ ይዤ ነው የሚያውቀኝ ሀገር
ዓለም ታየችኝ ባንቺ ውስጥ ሆና
በፍቅር ኩራዝ በላምባዲና
አሁን አየ ዐይኔ
አሁን አየ ዐይኔ
አሁን አየ ዐይኔ
አሁን አየ ዐይኔ
አሁን አየ ዐይኔ
ላምባዲና ላምባ
መሽቶ አይኔ በልጅነቴ
መርቃኝ ስትሞት እናቴ
/ወለል ወለል አለልኝ/
በፍቅር ብራ እንዳለችኝ
አንቺ ላይ ወስዳ ጣለችኝ
ላምባዲና
የእምዬ ሰምሮ ትንቢቷ
ወዳጅ አገኘሁ ካንጀቷ
/ወለል ወለል አለልኝ/
ኩራዜ ልክ እንደማዬ
አንቺ ነሽ ላምባዲናዬ
ላምባዲና ላምባዲና
ላምባዲና ላምባዲና
ላምባዲና ሆንሽለት ላይኔ ላይኔ መብራት
ላምባዲና ሆንሽለት ላይኔ ላይኔ መብራት
ላምባዲና ላምባ
እንዳትኮራበት ዐይንህን
ፍቅር ያልነካው ልብህን
/ወለል ወለል አለልኝ/
በማየት ስለማትበልጠኝ
ና መነጽሬን ለውጠኝ
ላምባዲና
ፍቅር የሌለው አይናማ
ውጦታልና ጨለማ
/ወለል ወለል አለልኝ/
ሰው ወዶ ሰው ያልወደደው
ምርኩዜን መጥቶ ይውሰደው
ላምባዲና
ላምባዲና ላምባዲና
ላምባዲና ላምባዲና
ላምባዲና ሆንሽለት ላይኔ ላይኔ መብራት
ላምባዲና ሆንሽለት ላይኔ ላይኔ መብራት
ያይኔ መቅረዙ ባዶ ነው
ማየት ለብቻው ምንድነው
ሳያይ ያመነ ሲጠራው
አይ ፍቅር መጥቶ ሲያበራው
ኦሆ……….
አሁን አየ አይኔ
አሁን አየ አይኔ
አሁን አየ አይኔ
አሁን አየ አይኔ

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO