LYRIC

ህልም መሳይ ፍጥረት ምትሀተኛ
ከሰው የተለየች ምናባዊ ምስል
ሰመመን ናት ደምቃ እየተቻለች
ሀያል ጥበብ ያላት የከበደ
ለማመን ያቃተ
ከላይ የተቻራት ልዩ ውበት
ታች አልተሸመተ
2X
በክፋት አለንጋ አሳስቃ አባብላ
መታ የማትረሳ
በህመሟ የሚድን ቂምን ሳያፈራ
ሳትጥል ጠባሳ
ሲዝት የዋለ በሷ ላይ
በቀል አልሞ ያነገተ
ሲያያት ይረሳል በደሏን
ፎክሮ ሄዶ ከሷጋር
ስትጫወት በእሳት ፈገል
ስታማልል በስስት አይታ
ስትረታ በፍቅር ይዛ
ስታሸንፍ በመልካም ፍቅር
ወይ አትከሰስ ወይ አትወቀስ
ወይ አትጠላ በልታ አትረሳ
2X
ህልም መሳይ ፍጥረት ምትሀተኛ
ከሰው የተለየች ምናባዊ ምስል
ሰመመን ናት ደምቃ እየተቻለች
ሀያል ጥበብ ያላት የከበደ
ለማመን ያቃተ
ከላይ የተቻራት ልዩ ውበት
ታች አልተሸመተ
መሬት ተለውሶ በእሾህ ተሸፍኖ
ዙሪያው የታጠረ
ተቀምሶ የማያልቅ ማር አለ በውስጧ
ሲጣፍጥ የኖረ
ሚስጥር ናት ቅኔ አትፈታ
በሰምና ወርቅ ተሰርታ
ህብረ ቀለም ናት ደማቅ
ህልም መሳይ ናት ድብቅ
አሳዝና ሺህ ጊዜ ክዳ
አትበላም ረግጣ ሄዳ
የማትታይ የማትጨበጥ
ከበደሏ ፍቅሯ የሚበልጥ
ወይ አትከሰስ ወይ አትወቀስ
ወይ አትጠላ በልታ አትረሳ
2X

Added by

Dibora Tadesse

SHARE

Comments are off this post

VIDEO